1 / 6
ስልጠናውን የሰጡት ድህረ ገጽን ባለሙት አቶ ያለውጊዜ ታደገኝ በደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ አይሲቲ ክፍል software developer and system ባለሙያ ድህረ ገፁ (Website) ለፍርድ ቤቱ የሚሰጠውን ጠቀሜዎችና አገልግሎቶች ለታዳሚዎች በዝርዝር ገለፃ ያደረጉ ሲሆን የሚከተለውን ጥቅም ከበዙ በጥቂቱ ያበረክታል ብለዋል፡፡
- ፍርድ ቤቱ የሚሰራቸውን ስራዎች ለህብረተሰቡ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ይጠቅማል፡፡
- የፍርድ ቤቱ አደረጃጀት ምን እንደሚመስል በቀላሉ ለመረዳት ያስችላል፡፡
- ተገልጋዩ ማህበረሰብ የተለያዩ ቅጻ ቅጾችን ወደ ፍርድ ቤት መምጣት ሳይጠበቅበት ባለበት ቦታ ሆኖ ድህረ ገጹን በማውረድ መጠቀም ይችላል፡፡
- በፍርድ ቤቱ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ቅሬታ ያለው አካል በአካል መቅረብ ሳይጠበቅበት ባለበት ቦታ ሆኖ ቅሬታውን እና ላቀረበው ቅሬታ ይጠቅመኛል የሚለውን የሰነድ ማስረጃ ለመላክ ያስችለዋል፡፡
- ማህበረሰቡ በፍርድ ቤቱ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለውን አስተያየት በቀላሉ ለመቀበል ያስችላል፡፡
- በፍርድ ቤቱ የሚወጡ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ ሲኖር ማስታወቂያውን ለመለጠፍ እንዲሁም አመልካቾች ባሉበት ቦታ ሆነው የቅጥር ፎርም ሞልተው ዶክመንታቸውን እንዲልኩ ያስችላል ብለዋል እንዴት መገልገል እንዳለብን ስለ አጠቃቀሙም ሰፊ ገለፃ አድርገዋል፡፡
ሌላው በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ እና የምንጠቀማቸውን ማህበራዊ ሚዲያዎች ከደህንነት አንፃር እንዲሁም እንዴት ማስተዳደር እንደሚቻልም ጭምር ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ አይሲቲ ክፍል software developer and system engineer ባለሙያ የሆኑት ያለውጊዜ ታደገኝ ላደረጉት አስተዋጽኦ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንቱ ክቡር አቶ ዮሐንስ ወንድሙ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡