North Shoa Zone Court
General

ጨካኝነት፣ ነውረኝነትና አደገኛነት በተሞላበት ሁኔታ የትዳር አጋሩን የገደለው ግለሰብ እድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተቀጣ

November 4, 2026 Verified Source / የተረጋገጠ Public Release / ሕዝባዊ መግለጫ
ጨካኝነት፣ ነውረኝነትና አደገኛነት በተሞላበት ሁኔታ የትዳር አጋሩን የገደለው ግለሰብ እድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተቀጣ
ከሳሽ፡- የሰሜን  ሸዋ ዞን ዐ/ህግ  መምሪያ 
ተከሳሽ፡-  ይትባረክ  አበበ  እድሜ 39 አድራሻ መሀል ሜዳ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ
ተከሳሽ  በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 539/1/ሀ/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ሰውን ለመግደል ጨካኝነት፣ ነውረኝነትና አደገኛነት በተሞላበት ሁኔታ የትዳር አጋሩን የገደለው ግለሰብ እድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተቀጣ
ከሳሽ፡- የሰሜን  ሸዋ ዞን ዐ/ህግ  መምሪያ 
ተከሳሽ፡-  ይትባረክ  አበበ  እድሜ 39 አድራሻ መሀል ሜዳ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ
ተከሳሽ  በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 539/1/ሀ/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ሰውን ለመግደል አስቀድሞ በማሰብ ጥቅምት 4/2018 ዓ/ም ከለሊቱ በግምት 7፡00 በሚሆንበት ጊዜ  መሀል ሜዳ ከተማ አስተዳደር 02 ቀበሌ ልዩ ስሙ ብሎክ 8 ከተባለው ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ውስጥ የትዳር ጓደኛው ሚስቱ የሆነችውን ሟች መሰረት አበበን ገንዘብ ወስደሽብኛል በማለት ቂም በመያዝ ከቤት ውስጥ በሩን ዘግቶ ጨካኝ፣ ነውረኛ እና አደገኛ መሆኑን በሚገልፅ ሁኔታ ከፌሮ ብረት በተሰራ የስጋ መከትከቻ መጥረቢያ አፏን፣ ጥርሷን፣አፍንጫዋን እና ራሷን መትቷት ከባድ ጉዳት አድርሶባት የገደላት በመሆኑ  ተከሳሹ በፈፀመው ከባድ የሰው ግድያ ወንጀል የሰሜን ሸዋ ዞን ዐ/ህግ መምሪያ በ2 የሰው ማስረጃ እና ተከሳሽ ለወረዳ ፍርድ ቤትና ለፖሊስ የሰጠውን የእምነት ቃል በማያያዝ በቀን 19/03/2018 ዓ/ም  ለሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት  የክስ ማመልከቻውን አቅርቧል፡፡
 
      ክሱ የቀረበለት የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ተከሳሹን ችሎት በማስቀረብ ክሡ በችሎት ተነቦለት እንዲረዳው ከተደረገ በኋላ የክስ ተቃውሞ ካለው የእምነት ክደት ቃሉን ሲጠየቅ የክስ ተቃውሞ የለኝም የወንጀል ድርጊቱን በተመለከተ አልፈጸምኩም በማለት ክዶ በመከራከሩ ዐ/ህግ ምስክሮቹን አቅርቦ አሰምቷል፡፡ ፍ/ቤቱም የዐ/ህግን ክስ፣ የምስክሮችን ቃል ከመረመረ በኋላ ተከሳሽ በተከሰሰበት  የወንጀል ህግ አንቀፅ 539/1/ሀ/ ላይ ተመለከተውን በመተላለፍ ከባድ የሆነ ሰው መግደል ወንጀል ጉዳይ ሊከላከል ይገባል በማለት በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ/142/1 መሰረት ፍ/ቤቱ ብይን የተሰጠ ሲሆን ተከሳሽም 1 መከላከያ ምስክር አቅርቦ ለፍርድ ቤቱ ጭብቱን በማስመዝገብ መከላከያ ምስክሩን ቃል  አሰምቷል፡፡ በመሆኑም ባቀረበው የመከላከያ ምስክር የዐ/ህግን ክስ ማስተባበል ባለመቻሉ  ዐ/ህግ ባቀረበው ክስ የወንጀል ህግ አንቀጽ 539/1/ሀ/  ስር የተመለከተውን የህግ ድንጋጌ በመተላለፍ ከባድ ሰው መግደል ወንጀል ጥፋተኛ ነው በማለት በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ/149/1 መሰረት ፍ/ቤቱ የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጥቷል፡፡
 
      የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት 23/02/2019 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ  ጥፋተኛ የተባለበት የወንጀል ህግ በተሻሻለው በአዲሱ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017  ላይ የቅጣት ደረጃ እና እርከን የወጣለት ሲሆን ለዚህ አድራጎቱ በደረጃ 2 እርከን 44 ላይ ያርፋል፡፡ በዐ/ህግ በኩል የቀረበ የቅጣት ማክበጃ በተመለከተ ተከሳሽ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው ሰውን ለመጉዳት ፍፁም ፍቃደኛ በመሆን በነውረኛነትና አደገኛነቱን የሚያሳይ ስለሆነ በወ/ህግ ቁጥ 84 መሰረት የቅጣት ማክበጃ ተይዞ አስተማሪ ውሳኔ ይሰጥልን ሲል አሳስቧል፡፡
 
የቅጣት ማቅለያን በተመለከተ በማስረጃ የተደገፈ 5 የተለያየ የቅጣት ማቅለያዎች የተያዘለት በመሆኑ ከእርከን 44 ወደ እርከን 39 ላይ ያርፏል፡፡ ሆኖም ተከሳሹ ጥፋተኛ የተባለው ከለሊቱ 7፡00 ሰዓት ላይ ከሚስቱ ጋር ተከራይተው ከሚኖሩበት ቤት ላይ ሚስቱ የሆነችውን በሩን ዘግቶ በስጋ መከትከቻ የተለያዬ ቦታ በመምታት  ጭካኔ እና ነውረኛ እንዲሁም አደገኛነቱን በሚያሳይ ሁኔታ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው በመሆኑ አጠቃላይ የወንጀል አፈፃፀሙ ሲታይ በጣም አደገኛ ከመሆኑ የተነሳ ቅጣቱ ባረፈበት እርከን ላይ ተከሳሹ ቢቀጣ የወንጀል ህጉን፣ የቅጣት አላማ እና ግብ የማያሳካ በመሆኑ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017 አንቀፅ 120 መሰረት በመመሪያው ውጭ ሊወሰን ይገባል በማለት ፍርድ ቤቱ  በተሰጠው ፍቅድ ስልጣን መሰረት ተከሳሹን ያርማል ፣ ያስተምረዋል እንዲሁም መሰል ድርጊት ፈፃሚዎችን ያስጠነቅቃል ብሎ ፍ/ቤቱ ባመነበት እድሜ ልክ ፅኑ እስራትና በወንጀል ህግ አንቀፅ 123 ና 124 መሰረት ከህዝባዊ መብቱ ለ5 አመት እንዲሻር ሲል ፍ/ቤቱ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
Share / አጋራ
Document Reference
  • Ref: FBC-8
  • Published: 13:25 · Nov 04, 2026
  • Integrity: SHA-256 Verified
Official Seal

This dispatch is sourced directly from the authorized channel. Content integrity is cryptographically verified.


ይህ መግለጫ ከተፈቀደው የመገናኛ መስመር በቀጥታ የተገኘ ነው።