1 / 18
ሌላው በ2018 በጀት አመት ከከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ለፍትህ ስርዓቱ መሻሻል ውጤታማ ላደረጉ አጋር አካላት፣ በተለያየ ምክንያት ተቋሙን ለለቀቁ ሰራተኞች እውቅና ሰጥቷል፡፡
በመጨረሻም በ2018 በጀት አመት ከ32 ወረዳ ፍርድ ቤቶች በማወዳደር ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ የወጡ ወረዳ ፍርድ ቤቶችን እውቅ እና የምስጋና የምስክር ወረቀት የተበረከተላቸው ሲሆን 1ኛ ደረጃን የያዘው የባሶና ወራና ወረዳ ፍርድ ቤት፣ 2ኛ ደረጃን የያዘው የጣርማ በር ወረዳ ፍርድ ቤት እና 3ኛ ደረጃ የወጣው የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ፍርድ ቤት የእለቱ ተሸላሚዎች በመሆን የእለቱ መርሀ ግብሩ ተጠናቋል፡፡