North Shoa Zone Court
General

የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2019 በጀት አመት መደበኛ ስራውን በድምቀት አስጀመረ

October 23, 2026 Verified Source / የተረጋገጠ Public Release / ሕዝባዊ መግለጫ
የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2019 በጀት አመት መደበኛ ስራውን በድምቀት አስጀመረ
Thumbnail 1
Thumbnail 2
Thumbnail 3
Thumbnail 4
Thumbnail 5
Thumbnail 6
Thumbnail 7
Thumbnail 8
Thumbnail 9
Thumbnail 10
Thumbnail 11
Thumbnail 12
ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው ስራቸውን ሲያከናውኑ የቆዩ ሲሆን የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2019 በጀት አመት መደበኛ ስራ ማስጀመሪያውን በዛሬው እለት በድምቀት አክብሯል፡፡

በመረሀ ግብሩ ላይም የተከበሩ አቶ ወርቃለማሁ ኮስትሬ የደ/ብርሃን አስተዳደር ምክትል ከንቲባ የተከበሩ አቶ ዮሐንስ ወንድሙ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት እና ሌሎች የዞንና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

በስብሰባው ላይ የተከበሩ አቶ ዮሐንስ ወንድሙ ለተሰብሳቢዎች የእንኳን ደህና መጣችን መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በንግግራቸውም እንደገለፁት በክረምት የዳኞች እረፍት ምክንያት ፍ/ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው ውስን ስራዎችን ሲያከንውኑ ስለቆዩ እና ጥቅምት 02/2019 ዓ/ም ጀምሮ መደበኛ ስራቸውን የጀመሩ መሆኑን በይፋ ለማብሰር ነው ብለዋል፡፡
ሌላው የዚህ መድረክ አላማ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥን በማላቅ የህዝብ አመኔታን ማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ አፅኖት ሰጥቶ የሚሰሩበት መዳላድል እየፈጠረ በመሆኑ ተገልጋዩ ማህበረሰባችን ፍርድ ቤቶች መደበኛ ስራቸውን ለማሳወቅ እንዲሁም በ2018 ዓ/ም ፍርድ ቤቱ በጥንካሬ የተከናወኑ እና በእጥረት የተስተዋሉ አፈፃፀሞችን በመለየት በክፍተት የታዩ ጉዳዮች በ2019 በጀት አመት እንዳይደገሙ ለማድረግ ከዚህ መድረክ ግብአቶችን በመሰብሰብ እንዲሁም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የጀመራቸውን ሁሉን አቀፍ የለውጥ ስራዎች በየደረጃው የሚገኙ ፍርድ ቤቶችን እውን በማድረግ እና አሰራሩን በዘመናዊ ቴክኖሎጅ በመደገፍ የተገልጋዩን እርካታ ለማረጋገጥ ያለመ ነው ብለዋል፡፡

አክለውም ፍርድ ቤቶች ነፃና ገለልተኛ ሆነው ህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ተደራሽ የሆነ፣ጥራት ያለው፣ቀልጣፋ ወጭ ቆጣቢ፣በተገልጋዩ ዘንድ ተአማኒነትን ያተረፈ አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም አማራጭ የሙግት መፍቻ ስርዓቶችን ከማስፋት አንፃር የባህል ፍርድ ቤቶችን በሁሉም ወረዳዎችና በስራቸው በሚገኙ ቀበሌዎች በማደራጀት ወደ ስራ በማስገባት ከመቼውም በላይ ጥረት ተደርጓል ብለዋል

የተከበሩ አቶ ወርቃለማሁ ኮስትሬ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ላይ እንደገለፁት ፍርድ ቤቶች ለሁለት ወራት ዝግ ሆነው የቆዩ ሲሆን አሁን ላይ መደበኛ ስራቸውን ጀመሩበት እለት በመሆኑ እንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በንግግራቸውም ለአንድ ሀገር ሰላምና እድገት የፍርድ ቤቶች ሚና የላቀ መሆኑን ገልፀው ከተማ አስተዳደሩ ፍርድ ቤቶችን የመደገፍ፣ ስራዎችን በቅንጅትና በትብብር የሚሰራ መሆኑን በአፅንኦት አስገንዝበዋል፡፡

ሌላው በያዝነው በጀት አመት ተሻለ አፈፃፀም ኖሮት ለህብረተሰባችን ፍትህ እንዲሰጥ ክልሉ የጀመራቸውን የዲጅታላይዜሽን ስራዎችን በዞናችን ተግባራዊ እንዲሆኑ እኛም እናግዛለን ብለዋል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የእቅድ በጀት ክትትል እና ግምገማ ባለሙያ አቶ ሸጋው ወ/ጊወርጊስ የ2018 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀምና የ2019 በጀት አመት እቅድ በዝርዝር በመርሀ ግብሩ ላይ ለተሳተፉ ታዳሚዎች አቅርበዋል፡፡ ሌላው በ2018 በጀት አመት በዞኑ ውስጥ ባሉ በባህል ፍርድ ቤቶች አጠቃላይ የተሰሩ ስራዎችን ክቡር ዳኛ እና የባህል ፍርድ ቤት ፎካል ፐርሰን አቶ ትእዛዙ ጌታቸው ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ ከቀረበው ሪፖርት ላይ በመነሳት ታዳሚዎች በርካታ ሀሳብ አስተያየየትና ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡

መድረኩን መሩት ክቡር አቶ ወርቃለማሁ ኮስትሬ፣ክቡር አቶ ዮሐንስ ወንድሙና ክቡር አቶ ደመረ ቸሬ በጋራ የመሩት ሲሆን በመድረኩ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ክቡር ፕሬዚዳንቱ በችሎት ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ማጠቃለያው ላይ እንደገለፁት፣ ፍርድ ቤቱ በ2018 በጀት ዓመት ያከናወናቸው አፈጻጸሞች በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚኝ ጠቁመዋል፡፡ ለዚህም ማሳያው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክልሉ የሚገኙ ከፍተኛ ፍርድ ቤቶችን አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም አወዳድሮ የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የቅንጅትና የትብብር ስራ ውጤት በሆኑን በመድረኩ ገልፀዋል።
Share / አጋራ
Document Reference
  • Ref: FBC-5
  • Published: 07:25 · Oct 23, 2026
  • Integrity: SHA-256 Verified
Official Seal

This dispatch is sourced directly from the authorized channel. Content integrity is cryptographically verified.


ይህ መግለጫ ከተፈቀደው የመገናኛ መስመር በቀጥታ የተገኘ ነው።