North Shoa Zone Court
Announcement

አስደሳች ዜና የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ድህረ ገጽ (Official Website) አበለፀገ

June 26, 2026 Verified Source / የተረጋገጠ Public Release / ሕዝባዊ መግለጫ
አስደሳች ዜና የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ድህረ ገጽ (Official Website) አበለፀገ
Thumbnail 1
Thumbnail 2
Thumbnail 3
Thumbnail 4
Thumbnail 5
Thumbnail 6
Thumbnail 7
Thumbnail 8
Thumbnail 9
Thumbnail 10
Thumbnail 11
Thumbnail 12
Thumbnail 13
አስደሳች ዜና
የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ድህረ ገጽ (Official Website) አበለፀገ
ደ/ብርሃን ሰኔ 18/2018 ዓ.ም (ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት)
የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ይረዳው ዘንድ ይፋዊ ድህረ ገጽ (Official Website) አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ ይህን ድህረ ገጽ ያበለጸጉት በደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ አይሲቲ ክፍል software developer and system engineer ባለሙያ የሆኑት ያለውጊዜ ታደገኝ ናቸው፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ዮሐንስ ወንድሙ፣ የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አቀፍ ጉድኝት አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረ/ፕሮፌሰር መቅደስ ጌራወርቅ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ደ/ብርሃን ምድብ ችሎት እና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችና ሰራተኞች እንዲሁም የሰሜን ሸዋ ዞን ፍትህ መምሪያው ዐቃቢያነ ህጎች ተገኝተዋል፡፡ ይህንን ድህረ ገጽ ያበለጸጉት አቶ ያለውጊዜ ታደገኝ ድህረ ገፁ ለፍርድ ቤቱ የሚሰጠውን ጠቀሜዎችና አገልግሎቶች ለታዳሚዎች በዝርዝር ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ድህረ ገጹ (Website) የሚከተለውን ጥቅም ከበዙ በጥቂቱ ያበረክታል ብለዋል፡፡
- ፍርድ ቤቱ የሚሰራቸውን ስራዎች ለህብረተሰቡ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ይጠቅማል፡፡
- የፍርድ ቤቱ አደረጃጀት ምን እንደሚመስል በቀላሉ ለመረዳት ያስችላል፡፡
- ተገልጋዩ ማህበረሰብ የተለያዩ ቅጻ ቅጾችን ወደ ፍርድ ቤት መምጣት ሳይጠበቅበት ባለበት ቦታ ሆኖ ድህረ ገጹን በማውረድ መጠቀም ይችላል፡፡
- የተለያዩ ህጎችን በቀላሉ ማግኘት ያስችላል፡፡
- በፍርድ ቤቱ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ቅሬታ ያለው አካል በአካል መቅረብ ሳይጠበቅበት ባለበት ቦታ ሆኖ ቅሬታውን እና ላቀረበው ቅሬታ ይጠቅመኛል የሚለውን የሰነድ ማስረጃ ለመላክ ያስችለዋል፡፡
- ማህበረሰቡ በፍርድ ቤቱ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለውን አስተያየት በቀላሉ ለመቀበል ያስችላል፡፡
- በፍርድ ቤቱ የሚወጡ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ ሲኖር ማስታወቂያውን ለመለጠፍ እንዲሁም አመልካቾች ባሉበት ቦታ ሆነው የቅጥር ፎርም ሞልተው ዶክመንታቸውን እንዲልኩ ያስችላል፡፡
- ተገልጋዩ ማህበረሰብ የሚስተናገድበትን ቢሮ ሰው መጠየቅ ሳይጠበቅበት በቀላሉ ከድህረ ገጹ ላይ ማግኘት ያስችለዋል፡፡
በድህረ ገጹ ላይ ከተካተቱት ውስጥ ለአብነት ያህል፡-
- የፕሬዝደንቱ መልዕክት
- የንዑስ ጉባኤ አባላት
- የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የማኔጅመንት አባላት
- የፍርድ ቤቱ ታሪካዊ ዳራ
- አስተያየት መስጫ
- የፍርድ ቤቱ የስራ መዋቅር
- የፍርድ ቤቱ መገኛ ቦታ እና የቢሮ አቅጣጫ ጠቋሚ
- የተለያየዩ ፎርሞች፣ ሕጎች እና ቅሬታ ማቅረቢያ
- ዜና
- ፍርድ ቤቱ በስራ አፈጻጸሙ ስላገኛቸው እውቅናዎች
- AI/Artifical intelejence/
- የስራ ቅጥር ማመልከቻ ማስገቢያ ወዘተ
ተገልጋዮች ድህረ ገጽን በእንግሊዝኛ፣ በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በትግርኛ እና በሶማሊኛ ቋንቋ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አቀፍ ጉድኝት አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረ/ፕሮፌሰር መቅደስ ጌራወርቅ ይህንን ቴክኖሎጅ ለመጠቀም በመጀመሪያ ራሳችንን ለለውጥ ማዘጋጀት ያስፈልጋል ያሉት ረ/ፕሮፌሰር ይህ ድህረ ገፅ ተቋሙን አለማቀፋዊ የሚያደርግ እና አሰራራችንን የሚያቀላጥፍና የሚያዘምን አሰራር እንደመሆኑ መጠን ተከታታይ ስልጠናም ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ሌላው ድህረ ገጹ አስተያዬቶችና ግብአቶችን በመቀበል ወደፊት የበለጠ እየተሻሻለ የሚሄድ መካተት ያለባቸውም እየተካተተ የሚሄድ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በተደረገው ገለፃ ላይም በእለቱ የተገኙት ታዳሚዎች ስለለማው /ስለበለፀገው/ ድህረ ገፅ ሀሳብ አስተያዬታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ አይሲቲ ክፍል software developer and system engineer ባለሙያ የሆኑት ያለውጊዜ ታደገኝ ላደረጉት አስተዋጽኦ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንቱ ክቡር አቶ ዮሐንስ ወንድሙ ምስጋናቸውን አቅርበው ለአቶ ያለውጊዜ ታደገኝ የእውቅናና የምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ተገልጋዩ ማህበረሰብም ከዚህ በላይ ያሉትን አገልግሎቶች http/www.nszhcourt.gov.et በሚለው ድህረ ገጽ ማግኘት የሚችል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
Share / አጋራ
Document Reference
  • Ref: FBC-4
  • Published: 08:03 · Jun 26, 2026
  • Integrity: SHA-256 Verified
Official Seal

This dispatch is sourced directly from the authorized channel. Content integrity is cryptographically verified.


ይህ መግለጫ ከተፈቀደው የመገናኛ መስመር በቀጥታ የተገኘ ነው።