1 / 4
ደ/ብርሃን ግንቦት 21/2018ዓ/ም ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
በዛሬው እለት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው እና የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኤርሚያስ የማነብርሃን (ዶ/ር) ጨምሮ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትን በተገኙበት ወቅት የዞኑ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ የደ/ብርሃን ምድብ ችሎት እና የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ዳኞችና ሰራተኞች አቀባበል አድርገዉላቸዋል።
በመቀጠልም የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጀመራቸውን የዲጅታላይዜሽን ስራዎችን ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በጉብኝታቸውም ስማርት ችሎቶችን፣ የኢ ፋይሊንግ ስራዎችን፣ በግልጽ ችሎት የሚሰራባቸውን የችሎት አዳራሾች በማዘዋወር ጉብኝት አድርገዋል።
ክቡር ፕሬዚዳንት አቶ አለምአንተ አግደው እንደገለጹት እነዚህን በክልልና በዞን ተግባራዊ እየሆኑ ያሉ የውጥ ስራዎችን ወደ ወረዳ ፍርድ ቤትም ለማድረስ በስፋት እንሰራለን ብለዋል።