North Shoa Zone Court
General

የደብረ ብርሃን ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በአገልግሎት አሰጣጥና ቅሬታ አፈታት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

June 18, 2026 Verified Source / የተረጋገጠ Public Release / ሕዝባዊ መግለጫ
የደብረ ብርሃን ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በአገልግሎት አሰጣጥና ቅሬታ አፈታት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ
Thumbnail 1
Thumbnail 2
Thumbnail 3
Thumbnail 4
Thumbnail 5
Thumbnail 6
የደብረ ብርሃን ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በአገልግሎት አሰጣጥና ቅሬታ አፈታት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ
ደ/ብርሃን፣ ሰኔ 06/2018 ዓ/ም (ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት)
የደብረ ብርሃን ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ለዳኞች፣ የጉባኤ ተሿሚዎችና ለአስተዳደር ሰራተኞች በዛሬው እለት በጫጫ ከተማ በአገልግሎት አሰጣጥና ቅሬታት አፈታት ላይ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ በስልጠና ላይ የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ዮሐንስ ወንድሙ፣ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የማናጅመንት አባላት፣ የጫጫ ከተማ አስተዳዳሪ አቶ ደረሰ ደመመ ተገኝተዋል፡፡
በስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ዮሐንስ ወንድሙ ስልጠናውን አስመልክቶ ለሰልጣኞች መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልዕክታቸውም ተቋማት ተቀናጅተው ለባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠታቸው ለውጤታማ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ያለው አበርክቶ ቀላል አይደለም ብለዋል ይህንንም ስልጠና ያዘጋጁትን አካላት አመስግነዋል፡፡
ሌላው በስልጠናው ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የአንጎለላ እና ጠራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደረሰ ደመመ ባለፈው በጀት አመት የዳኝነት የሚሰጥበት እና ህዝብ የሚገለገልበት ተቋም የዳኝነት ስራውንና ህዝቡን የሚመጥን ቢሮ ባለመሆኑ በጀቱን የከተማው አስተዳደር በመቻል በ90 ቀናት ቢሮ አስገንብተን ምቹና ውብ የሆነ የችሎት አዳራሽ አሰርተን ለፍርድ ቤቱ ያስረከብን መሆኑይ ታወቃል፡፡ ይህ መደረጉ የወረዳችን ማህበረሰብ በተሻለ ቢሮ እንዲስተናገድ ጥሩ መደላድል ፈጥሯል ብለዋል፡፡ በቀጣይም ይህንን ስራዎችን አጠናክረን እናስቀጠለለን ብለዋል፡፡
የእለቱን ስልጠና የሰጡት የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች አስተዳደር ንዑስ ጉባኤ ፅ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ይርጋ ደጀኔ በአገልግሎት አሰጣጥና ቅሬታ አፈታት ላይ የስልጠና ሰነድ በማዘጋጀት አሰልጥነዋል፡፡
ከስልጠናው በኋላም ሰልጣኞችን ክቡር ፕሬዚዳንቱ ያወዩ ሲሆን ከስልጠናው በተገኘው ግብአት ወደ ተቋማችን የሚመጡ ማህበረሰብ በመልካም ስነ-ምግባር በታማኝነትና በቅንነት ማገልገል አለብን ሲሉ አስሳበዋል ሌላው በሚስተዋሉ ክፍተቶችም ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል ከሰልጣኞችም በርካታ በስራ ላይ ያጋጠሟቸውን ችግሮች አንስተው ምላሽና ማብራሪያ ክቡር ፕሬዚዳንቱ ሰጥተዋል በቀጣይም መሰራት ያለባቸውን ሁሉም ሀላፊነትን ወስዶ መስራት እንዳለባቸውም ጭምር አሳስበዋል፡፡
ስልጠናው በሰልጣኞች ላይ ከፍተኛ የሆነ መነቃቃት የፈጠረ እና ወደፊትም እንደዚህ ያሉ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ቢሰጡ ቀልጣፋ፣ ተደራሽ፣ ተገማች እና የሕዝብ አመኔታ ያተረፈ አግልግሎት ለማህበረሰቡ ለመስጠት እንደሚያስችል ሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
Share / አጋራ
Document Reference
  • Ref: FBC-1
  • Published: 08:35 · Jun 18, 2026
  • Integrity: SHA-256 Verified
Official Seal

This dispatch is sourced directly from the authorized channel. Content integrity is cryptographically verified.


ይህ መግለጫ ከተፈቀደው የመገናኛ መስመር በቀጥታ የተገኘ ነው።